News News

የበርበራ ወደብ የኮንቴነር ተርሚናል በይፋ ስራ ጀመረ

የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ፣ የኢፌዴሪ ከፍተኛ ልኡካን እና የዲፒ ወርልድ ዳይሬክተር ሱልጣን ቢን ሱለይማን በተገኙበት የበርበራ ወደብ የመጀመሪያ ዙር ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመርቆ በይፋ ስራውን ጀምሯል። በዲፒ ወርልድ 51%፣ በሶማሊላንድ 30% እና በኢትዮጵያ 19% ሼር የተያዘው የበርበራ ተርሚናል ኮርደር የመጀመሪያ ዙር ማስፋፊያ ፕሮጀክት 500 ሺህ ኮንቴነሮችን መያዝ የሚችል ተርሚናል እንደሆነና በአመት አንድ ሚልዮን ኮንቴነሮችን ማስተናገድ ይችላል ተብሏል። ወደቡ ዘመናዊ ክሬኖች እንደተገጠሙለትና ከዛሬ ጀምሮ ግዙፍ መርከቦችን በማስተናገድ ለቀጠናው በተለይ ለኢትዮጵያ ትልቅ ጥቅም እንዳለው ተገልጿል።

የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ።

ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በአገራችን ቀዳሚ እና በአይነቱም ሆነ ስፋቱ እንዲሁም ዘመናዊነቱና የአረንጓዴ ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት ተምሳሌት እንደሚሆን በሚጠበቀው የሞጆ ደረቅ ወደብ መሰረተ ልማት ማሻሻያ የግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓት በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲ ቀዳሚ ትኩረት ካገኙ አበይት የዘርፉ ጉዳዮች ውስጥ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት ግንባታን በጥራት፣ በአይነትና በመጠን ማስፋፋትና በላቀ አሰራር እና ቴክኖሎጂ የታገዙ ማድረግ አንዱ ነው ብለዋል። በፖሊሲው የደረቅ ወደብ ልማትና አገልግሎትን ለግል ባለሃብቶች ጭምር ክፍት የማድረግ፣ በደረቅ ወደቦች የጋራ አጠቃቀም (Common Use Facility) አሰራር በመዘርጋት በመንግስት የተገነቡ ደረቅ ወደቦች ውስጥ የግል ባለሃብቶች ገብተው አገልግሎት የሚሰጡበት አሰራር የማምጣት እና ደረቅ ወደቦችን በጋራ (Joint Investment) በመንግስትና የግል ዘርፍ በጋራ የማልማትና ማስተዳደር ፍላጎቶችን እና አቅጣጫዎችን በግልጽ ማመላከቱን ግልጸዋል፡፡

የሎጀስቲክስ ዘርፉን ከማዘመን አንጻር የሚታዩ ጉድለቶችን በመለየት መሙላት ላይ መሠረት ያደረገ የጥናት ሰነድ ላይ ዉይይት ተደረገ።

የዉይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት በኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኢ/ር የኋላእሼት ጀመረ ሲሆኑ የሎጀስቲክስ ዘርፉን ከማዘመን አንጻር እየታዩ በሚገኙ ክፍተቶች ላይ የተደረገዉ ጥናት በሚኒስቴር መ/ቤቱ ተግባራዊ እየተደረገ ያለዉን ብሔራዊ የሎጀስቲክስ ፖሊስና ስትራቴጂዎችን በተሻለ ዉጤታማነት ተግባራዊ ለማድረግ ያግዘናል ብለዋል።

የመንገድ ደህንነት ትምህርትን በሁለተኛ ዲግሪ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማስተባበር የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል:: የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው ደረጃ ለመቀነስ ቀዳሚ ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ በዘርፉ ላይ ዕውቀት ያላቸውን ባለሙያዎች ማፍራት ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ የመንገድ ደህንነት ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የፊርማ ስነ ስርዓት አድርጓል፡፡

የመንገድ ደህንነት ትምህርት በሀገራችን ስርዓተ ትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራፊክ አደጋ በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ 1.35 ሚሊየን ሰዎችን ሕይወት እያሳጣ መሆኑን ገልጸዉ 90 በመቶው አደጋ ሚከሰተዉም መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸዉ ሃገራት ላይ መሆኑን አብራርተዋል። በመልዕክታቸዉም በሃገራችን አብዛኛዉ የህብረተሰባችን ክፍል ወጣት እንደመሆኑ የትራፊክ አደጋ በሰብአዊ ልማታችን፣ በእድገት መስመራችንና በሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞአችን አሉታዊ ተጽኖ እየፈጠረ የሚገኝና ከምንም በላይ እጅግ ውድ የሆነውንና በምንም የማይተካውን የሰው ልጅ ሕይወት እያሳጣን የሚገኝ ስንክሳር ሆኖ እናገኘዋለን ብለዋል፡፡

ከ600 ሚልዮን ብር በላይ የተገዙ የተለያዩ ለመንገድ ጥገና የሚውሉ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተበረከተ።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከመንገድ ፍንድ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ የተገዙና ለመንገድ ጥገና የሚውሉ የተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች የርክብክብ ሥነሥርዓት ላይ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ ፣ ክብርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ ክቡራን የሚንስትር ዴኤታዎች፣ የክልል እና የከተማ አሰትዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት ለመንገድ ግንባታ የምንሰጠው ያክል ትኩረት ለመንገዶች እንክብካቤም ማድረግ አለብን ያሉ ሲሆን ከመንገድ ጥገና ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ትልቅ ሚና የሚኖረው የክልል እና የከተማ አስተዳደር የመንገድ ኤጀንሲዎች አቅም ለመገንባት በትራንስፖርት ዘርፍ 10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ በተያዘው መሠረት የተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ማስረከብ በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።