አስተዳደራዊ አወቃቀር
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጽ/ቤት አደረጃጀትና አሠራር
የም/ቤቱ ጽ/ቤት የተቋቋመበት ዋናው ዓላማ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በከተማ አስተዳደሩ ቻርተር የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር በአግባቡ እንዲያከናውንና ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማስቻል በማስፈለጉ፤
የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት በተሻሻለው የከተማ አስተዳደሩ ቻርተር አዋጅ ቁጥር ፫፻፷፩/፲፱፻፺፭ ዓ.ም አንቀፅ 14 (2) (ሠ)መሠረት ህጋዊ ሰውነት ያለው ሆኖ በህግ ማቋቋም በማስፈለጉ፤
የም/ቤቱ ጽ/ቤቱ ተግባር
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 34 /2004 ተቋቁሟል፡፡
- የም/ቤት ጽ/ቤት በከተማ ደረጃ በዋናነት ሲገኝ በክ/ከተማና የወረዳ ም/ቤቶች በጽ/ቤት ደረጃ አልተዋቀሩም
- በክ/ከተማና በወረዳ ደረጃ አሰራሩ የተዘረጋ ሲሆን በከተማ በቀድሞው 3 ዋና የሥራ ሂደቶችና 5 ደጋፊ የሥራ ሂደቶች፤ እንዲሁም 2 የስራ ክፍሎች እና በ1 ቡድን ተዋቅረው የነበረ ሲሆን በአዲሱ የነጥብ ስራ ምዘና ምዘናና የደረጃ አወሳሰን ዘዴ (ጄኢጂ) በ8 ዳይሬክቶሬቶች ተደራጅቷል፡፡ ይህ መዋቅርም በክ/ከተማ ደረጃ በ3 ቡድን እንዲሁም በወረዳ በ2 ቡድን የተደራጀ ነው፡፡
- የከተማው ም/ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ በሹመት የሚመደብ ሲሆን ተጠሪነቱ ለአፈ-ጉባኤው ነው፡፡
- የም/ቤቱ ጽ/ቤት ኃላፊ የአስተባባሪ ኮሚቴው አባል ነው፡
- በም/ቤቱ ጽ/ቤት የሚገኙ ሁሉም ዳይሬክተሮች ተጠሪነታቸው ለም/ቤቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ፡፡
- የም/ቤቱ ጽ/ቤት ባለሙያዎች የቅጥር ሁኔታ በሲቪል ሰርቪስ ህጎች መሰረት የሚፈፀም ነው፡፡
- ለፅ/ቤቱ የሚመደበው በጀት በም/ቤቱ ቀርቦ እንደሌሎች ሴክተር ቢሮዎች በጋራ የሚጸድቅ ነው፡፡
- በአዲሱ የሥራ ሂደት ጥናት መሠረት የከተማው ም/ቤት ጽ/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎችንና ም/ቤቱን በሚደግፍ ሁኔታ የተዋቀረ ሲሆን በተመሳሳይ
- በክ/ከተማና በወረዳም የአሰራር ስርዓቱ ተዘርግቷል፡፡
- በም/ቤት ጽ/ቤቱ የፕሮሰስ ካውንስል በጽ/ቤቱ ኃላፊ የሚመራ ሲሆን በየ 15 ቀኑ የግንኙነት ጊዜ አለው፡፡ከክፍለከተማ ጋር በየወሩ የግንኙነት ጊዜ አላቸው፡፡
ገጾች: 1 2